Saturday, December 17, 2011

የዋሽንግተን ዲሲ ዲሲና አካባቢው ሀገረ ስብከት አቡነ አብርሃምን ሸኝቶ አቡነ ፋኑኤል ሊቀበል ነው

  














·  በብፁዕ አቡነ አብርሃም መሔድ ብዙዎ አዝነዋል።
·  አቡነ ፋኑኤል በመመደባው ተቃውሞው በየሥፍራዉ እየቀጠለ ነው።
·  አቡነ ፋኑኤልን ከሕዝብ ለማቀራረብ መሐል ሰፋሪው ቡድን ደፋ ቀና እያለ ነው።

(ኖላዊ ዘተዋሕዶ፤ታህሳስ 72004)-ላለፉት ስድስት ዓመታት የኒዉዮርክ እና አካባቢው እንዲሁም የዋሽንግተን ዲሲ እና  አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በመሆን ሲያገለግሉ የቆዩት ብፁዕ አቡነ አብርሃም ወደ አዲሱ ሀገረ ስብከታቸው ወደ ሐረር ለመሄድ በዝግጅት ላይ ናቸው።ለብፁፅነታው ሽኝት መርሐ ግብር ለማዘጋጀት በሀገረ ስብከታቸው ሥር የሚገኙ ወጣቶች እና ካህናት እየተሰናዱ ነው።እንደ ብዙዎች እምነት ብፁዕነታቸው ከወጣቱ ጋር ተጋባብቶ በማስራትና በሃይማኖት ጉዳይ ጠንካራ  ነበሩ።ወቅቱ የተሐድሶ እንቅስቃሴ የተስፋፋበት ቤተ ከርስቲያን ከባድ ፈተና ላይ ያለበችበት እንደመሆኑ ብፁዕ አቡነ አብርሃምን የመሰለ አባት ማጣት እጅጉን እንደሚከብድ አብዛኛው ወጣት በሀዘን ይገልጻል።

በሌላ በኩል የብፁዕ አብርሃምን ወደ ሀገር ቤት መሄድ ተከትሎ ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል የዋሽንግተን ዲሲን ሀገረ ስብከት ከካሊፎርኒያ ሀገር ስብከት ጋር ደርበው እንዲይዙ በተወሰነላቸው ውሳኔ መሠረት ሥራ ለመጀመር ደፋ ቀና እያሉ ነው።አቡነ ፋኑኤል ከነ በጋሻዉ ደሳለኝ ጋር በመሰረቱት የቆሎ ባልነጀራነት ሳቢያ ተቃውሞን ማስተናገድ ከጀመሩ እንደሰነበቱ የአደባባይ ምስጢር ሲሆን  አዋሳ ላይ በተነሳባተው የሕዝብ ተቃውሞ ሀገረ ስብከቱን በሃይል እንደለቀቁ የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው።ጥፋታቸውን ከማረም ይልቅ ተቀውሞውን ማኅበረ ቅዱሳን ያቀናበረው እንደነበር  የሚናገሩት አቡነ ፋኑኤል ሌላ የታሪክ ስሕተት ለመድገም አሁንም አየተዘጋጁ እንደሆነ መረጃዎች ይጠቁማሉ።
በስራቸው ለሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት ደብዳቤ በማብረር የስብሰባ ጥሪ ያስተላለፉት ሊቀ ጳጳሱ የመጀመሪያ ስብሰባ በዋሽንግተን ዲሲ ለማድረግ  ዝግጅታቸውን አጠናቀዋል።በሌላ በኩል ይህ ስብሰባ ከመደረጉ ቀድም  ብሎ በዋሽንግተን ከአስራ አራት ያላነሱ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት  ተባብሮ ለመስራት ፈቃደኞች አለመሆናቸውን አሳውቀዋል።በካሊፎርንያም በተመሳሳይ  ሁኔታ በርካታ ቁጥር ያላቸው አብያተ ክርስቲያናት ተቃውሞ ማሰማት ጀምረዋል።አንዳንዶቹም ሊቀ ጳጳሱ በጠሩት ስብሰባ ላይ ተገኝተው ተቃውሞ ለማሰማት ተዘጋጅተዋል::
በዲሲ አካባቢ የሚገኝ ከኢትዮጵያም አጋር ያለው እና መሐል ሰፋሪ እንደሆነ የሚነገርለት የሰባክያን ቡድን  አቡነ ፋኑኤልን ከሕዝብ ለማቀራረብ የአዋሳው ታሪክ እንዳይደገም ለማድረግ የመንገድ ጠራጊነት ስራውን መሥራቱን ተያይዞታል::“ተሐድሶ” የሚባል ነገር የለም  ከሁሉም ጋር አብረን መሥራት አለብን የሚል አቋም ያለው ይህ ቡድን እነበጋሻው ደሳለኝን አሳደደ በሚል ማኅበረ ቅዱሳንን ለመተናኮል እየተዘጋጀ  እንደሆነም ውስጥ አዋቂዎች ይጠቁማሉ።
                                                      መልካሙን ያሳየን

No comments:

Post a Comment